እኛ ማን ነን፡ እኛ ማን ነን? እኛ የሱሪ ህዝቦች ነን። የምንኖረው በደቡብ ምዕራብ የኢትዮጵያ ክፍል ነው።
የሱሪ ህዝብ በሶስት ጎሳዎች የተዋቀረ ሲሆን እነርሱም ቻይ፣ ቲርማጋ እና ባሌ ናቸው።
የቻይ ጎሳ መሪዎች ሶስት ናቸው፥ እነርሱም ዶሎቴ፣ ኤከዲ እና ሃላጋሜሪ ይባላሉ። በ አሁን ጊዜ የሚመራቸው ግን ዶሎቴ ነው።
የቲርማጋ ጎሳ መሪዎች አምስት ናቸው። እነርሱም ቦሎጊዳንጊ፣ ኦሌዞጊ፣ ኦሌሲርዋ፣ ቤባላ እና ኦሊኛሜሪ በመባል ይታወቃሉ። በአሁን ጊዜ መሪያቸው ቦሎጊዳንጊ ነው።
የባሌ ጎሳ መሪዎችም አምስት ናቸው። እነርሱም ዳላላ፣ ሚሮሊንጎ፣ ማሆሊ፣ ሲሪያሊ እና ዎሲ በመባል ይታወቃሉ። በአሁን ጊዜ መሪዎቻቸው ዳላላ እና ሚሮሊንጎ ናቸው።
በአጠቃላይ አሁን የሱሪ ህዝብ አራት መሪዎች አለው።ለ ቻይ ዶሎቴ፥ ለቲርማጋ ቦሎጊዳንጊ፥ ለ ባሌ ደግሞ ሁለት፥ ዳላላ እና ሚሮሊንጎ።
የሱሪ ህዝብ በአብዛኛው ከብት አርቢ ሲሆን፥ ገበሬዎችም አሉ።
ስለእኛ ነገሮችን የምንለጥፍበት ቦታ ይህ ነው። እዚህ ያሉን ነገሮች ስለ ሱሪ ልማዶች እና ጎሳዎቻችን፣ ዜናዎች፣ የትምህርት ቤት መጽሃፎች፣ ቪዲዮዎች፣ የድምጽ ቅጂዎች፣ የሱሪ ቅዱሳት መጻህፍት፣ ስለ ሱሪ ቋንቋ እና ፊደል፣ ፎቶዎች እና ሌሎች ነገሮች ናቸው።
ቻይ
ትርማጋ
ባሌ